Fana: At a Speed of Life!

ፊንላንድ ለቀጣዩ ሃገራዊ ምርጫ ማስፈጸሚያ የሚውል የ800 ሺህ ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመች

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 29 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፊንላንድ ለቀጣዩ ሃገራዊ ምርጫ ማስፈጸሚያ የሚውል የ800 ሺህ ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመች።

የድጋፍ ስምምነቱን በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር ሄሌና ኤራክሲነን እና የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት ተወካይ ቱርሃን ሳልህ ተፈራርመውታል።

ድጋፉ የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት በኢትዮጵያ ዴሞክራሲን ለማጠናከርና ቀጣዩን ምርጫ ግልጽና ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲካሄድ ለጀመረው ፕሮጀክት የሚውል ነው።

ፕሮጀክቱ ቀጣዩ ምርጫ ሁሉን አሳታፊ፣ ግልጽ እና ተዓማኒ ለማድረግ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድን አቅም ለማሳደግ ያለመ ነው።

አምባሳደር ሄሌና ቀጣዩ ምርጫ ለኢትዮጵያ እጅግ ወሳኝ መሆኑን በፊርማ ስነ ስርዓቱ ወቅት ተናግረዋል።

አያይዘውም ፊንላንድ በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ምርጫ ተዓማኒ እና ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲካሄድ የሚደረገውን ጥረት በማገዟ ደስተኛ መሆኗንም ገልጸዋል።

መረጃው በአዲስ አበባ የፊንላንድ ኤምባሲ ነው፤

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.