Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ያገኙት የኖቤል የሰላም ሽልማት ሜዳሊያና ዲፕሎማ ቅጂ በብሔራዊ ሙዚየም የማስቀመጥ ስነ ስርዓት ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ያገኙት የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት ቅጂ ሜዳሊያና ዲፕሎማ በብሔራዊ ሙዚየም የማስቀመጥ ስነ ስርዓት ተከናወነ።

የማስቀመጥ ስነ ስርዓቱ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና ታዋቂ ግለሰቦች በተገኙበት ነው የተከናወነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ያገኙት የኖቤል የሰላም ሽልማት ቅጂ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ በሰላም ሚኒስቴር እና በብሄራዊ ሙዚየም እንዲቀመጥ ተደርጓል።

የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚልም የኖቤል የሰላም ሽልማቱን ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ለቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣንና ብሄራዊ ሙዚየም የስራ ሃላፊዎች አስረክበዋል።

ብሄራዊ ሙዚየም ሃገሪቱ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች ያለፈችባቸውን አጋጣሚዎች የሚያሳይ መሆኑን ጠቅሰው፥ ሽልማቱ በሙዚየሙ መቀመጡ የታሪክ አጋጣሚውን ከማሳየት ባለፈ የጎብኝዎች መስህብ ይሆናል ብለዋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሽልማቱን ባስረከቡበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ደግሞ፥ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባልተቋረጠ ሂደት የጥናትና ምርምር የሚካሄድበት በመሆኑ ሽልማቱ በሌሎች ዘርፎች ውጤት ለማስመዝገብ ይጠቅማል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና በበኩላቸው ሽልማቱ፥ የዩኒቨርሲቲውን ስም ከፍ እንደሚያደርገው ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ 100ኛውን የዓለም የሰላም ኖቬል ሽልማት አሸንፈው ሰሞኑን ሜዳሊያውንና ዲፕሎማውን መቀበላቸው የሚታወስ ነው፡፡

በሀብታሙ ተክለስላሴ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.