Fana: At a Speed of Life!

የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ የኖቤል ሽልማት በመጪው እሁድ በብሔራዊ ሙዚየም ይቀመጣል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ያገኙት የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት አንደኛው ሜዳሊያና ዲፕሎማ በብሔራዊ ሙዚየም እንዲቀመጥ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ይህንን ተከትሎ የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት በመጪው እሁድ በብሔራዊ ሙዚየም እንደሚቀመጥ የኢትዮጵያ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ 100ኛውን የዓለም የሰላም ኖቬል ሽልማት አሸንፈው ሰሞኑን ሜዳሊያውንና ዲፕሎማውን መቀበላቸው የሚታወስ ነው፡፡

ሽልማቱ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና ታዋቂ ግለሰቦች በተገኙበት ይቀመጣል ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.