Fana: At a Speed of Life!

የዓለማችን ጥልቅ ስፍራ በአንታርክቲካ ተገኘ

በበረዷማው ክፍል የተገኘው ጥልቅ ስፍራ ከባህር ጠለል በታች 3 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ጥልቀት አለው ነው የተባለው።

አሁን በተመራማሪዎች የተገኘው ጥልቁ ስፍራ ከፈረንጆቹ 1967 ጀምሮ በተደረገ ጥናት የተለየ ነው ተብሏል።

ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና የምርምር ማዕከላት የተውጣጡት ተመራማሪዎችም በበረዶ ግግር በተሸፈነው አካባቢ ጥልቁን የምድራችን ክፍል ማግኘታቸውን ገልጸዋል።

ይህ ደግሞ ትልቁ የበረዶ ንጣፍ ምን ያህል መሳሳቱን ማሳያና በርካታ መጠን ያለው የበረዶ ግግር ቀልጦ በጠባቡ የባህር ክፍል ወደታችኛው መውረዱን ማሳያ ነው ተብሏል።

በአንታርክቲካ እና በደቡባዊው የምድር ዋልታ የሚገኘው የበረዶ ግግር ቀጣይ እጣ ፋንታ ላይ አስጊ ሁኔታ ስለመደቀኑ ማሳያም ነው ተብሏል።

ተመራማሪዎቹም አሁን የተገኘው ጥልቅ ስፍራ የአየር ንብረት ለውጥ ያሳደረው ተፅዕኖ ማሳያ ነው ብለውታል፥ የደቡብ ዋልታ መጻኢ ሁኔታም አስጊ ሁኔታ እንደተደቀነበትም ይገልጻሉ።

ሙት ባህር በንፅፅር የምድራችን ጥልቅ ስፍራ ሊገኝ የሚችልበት አካባቢ መሆኑ ይነገራል፤ አካባቢው ከባህር ጠለል በታች 413 ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.