Fana: At a Speed of Life!

የእርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላት ከአማራ ክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የእርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላት ከአማራ ክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በሰላም እና ደህንነት ዙሪያ ውይይት እያደረጉ ነው።

በውይይት መድረኩ ላይ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ላቀ አያሌው፣ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ሰብሳቢ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌል፣ ምክትል ሰብሳቢ ወይዘሮ የትነበርሽ ንጉሴ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ምክትል ሰብሳቢ ወይዘሮ የትነበርሽ ንጉሴ፥ የኮሚሽኑ ዋነኛ ዓላማ ግጭቶች ዳግም እንዳይፈጠርሩ ህክምና በማድረግ የዜጎችን ሠላም ማስጠበቅ እንደሆነ ነው የተናገሩት።

የእርቀ ሰላም ኮሚሽሹ ከዚህ በፊት በአሮሚያ፣ በትግራይ፣ እና በጋምቤላ ክልል እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት መደረጉንም አንስተዋል።

የእርቅ ሰላም ኮሚሽኑ በግጭት ለተጎዱ የህብረተብ ክፍሎች መድርስ እና እውቅና መስጠት ዋና ለአላማ መሆኑንም ነው ምክትል ሰብሳቢዋ የተናገሩት።

የእርቀ ሰላም ኮሚሽኑ ለውጤታማነቱ በህበረተሰብን እያሳተፈ መሆኑን በመጥቀስ ከህብረተሰብ ተወካዮች እና ከክልል አመራሮች ጋር ውይይቱ ይቀጥላል ብለዋል።

የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ላቀ አያሌው በበኩላቸው፥ ውይይት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የሰላም የኖቤል ሽልማት በተቀበሉበት እንዲሁም ጥምቀት በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት በተመዘገበበት ማግስት መደረጉ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

በናትናኤል ጥጋቡ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.