Fana: At a Speed of Life!

የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ከሱዳን መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የተመራ ልዑክ ከሱዳን መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ሚኒስትር ሃሺም ኢብነኦፍ ሱሌይማን ጋር ተወያይቷል፡፡

በውይይቱ ወቅት በሃገራቱ የትራንስፖርት ዘርፍ ዙሪያ መክረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በሃገራቱ መካከል ስላለው የትብብር ደረጃ እንዲሁም በወደብ አጠቃቀም እና በዘርፉ የተደረጉ ስምምነቶችን ለመተግበር እየተከናወኑ በሚገኙ ሥራዎች ዙሪያ መምከራቸውን በሱዳን ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በሚኒስትሯ የተመራ የልዑካን ቡድን ትናንት ካርቱም መግባቱ ይታወሳል፡፡

የልዑካን ቡድኑ ካርቱም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የሱዳን የትራንስፖርት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሞዌ አሊ ካሊድ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.