Fana: At a Speed of Life!

አዛውንቷ በ80 ዓመታቸው ከዩኒቨርሲቲ በመመረቅ ህልማቸውን አሳክተዋል

ዶንዜላ ዋሽንግተን የተባሉት አዛውንት ኮሌጅ በመቀላቀል በ80 ዓመታቸው በሶሻል ወርክ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ማግኘት ችለዋል።

አዛውንቷ ይህን ጉዞ ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ፍላጎታቸውን ለማሳካት እንደጀመሩት ጠቅሰው፥ በአዝናኝ መልኩ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ እንደነበርም ገልጸዋል።

የእርሳቸው ህልምን የማሳካት ጉዞ ሰዎች መቸም ቢሆን በጀመሩት ነገር ላይ ተስፋ እንዳይቆርጡ ለማሳየት ያለመ መሆኑንም ያስረዳሉ።

ወጣት እና ጎልማሶችን ሲመለከቱ እንደሚነሳሱ የሚገልጹት አዛውንቷ፥ ህልም ካለ ያን ህልም ከግብ ማድረስና ማሳካት ያስፈልጋል ብለዋል፤ ያንን ለማድረግም በራስ ማመን እንደሚገባ በመጥቀስ።

ልጃቸው ኪምበርሊ ደግሞ ወላጅ እናቷ ለአላማቸው መስዋዕትነትን የከፈሉ የጥንካሬ እና የቁርጠኝነት ምሳሌ መሆናቸውን ትገልጻለች።

የ80 ዓመቷ አዛውንት የአሁኑ ጉዞ መጀመሪያ እንጅ መዳረሻ አለመሆኑን በመጥቀስ፥ በቀጣይ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን እንደሚይዙ ገልጸዋል።

 

 

ምንጭ፦ rocketcitynow.com/

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.