Fana: At a Speed of Life!

በባህር ዳር ከተማ 449 ህገ ወጥ ሽጉጦች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በባህር ዳር ከተማ 449 ህገ ወጥ ሽጉጦችና የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ።

በባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ ሰማዕታት አካባቢ ከአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ 449 ህገ ወጥ ሽጉጦች መያዛቸውን የአማራ ክልል የሰላምና የህዝብ ደህንነት ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።

ህገ ወጥ መሳሪያዎቹ የተያዙት የባህርዳር አድማ ብተና ፖሊስ ከአምስተኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ በቅንጅት በፈፀሙት ተግባር መሆኑ ተገልጿል።

ጉዳዩን ከምንጩ ለማረጋገጥ የምርመራ ቡድን ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.