Fana: At a Speed of Life!

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ ልዑክ በስደተኞች ፎረም ላይ እየተሳተፈ ይገኛል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የመንግስት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በዓለም አቀፉ የስደተኞች ፎረም ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጄኔቫ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በኢትዮጵያ ሚሲዮን አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

አቶ ደመቀ በፎረሙ ላይ ንግግር የሚያደርጉ ሲሆን፥ መቀመጫቸውን ጄኔቫ ካደረጉ ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ድጋፍ ሰጭ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ይወያያሉ ተብሎም ይጠበቃል።

በፎረሙ ላይ የልዑካን ቡድኑ ኢትዮጵያን በመወከል ከስደተኞች ጋር በተያያዘ በሰብዓዊ ድጋፍ አገልግሎት ዙሪያ የሃገሪቱን ተሞክሮ እንደሚያጋራ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ በቀዳሚነት ስደተኛ ተቀባይ ሃገር ከመሆኗ ጋር ተያይዞ አፍሪካን በመወከል በፎረሙ ላይ በብቸኝነት እንድትሳተፍ መመረጧን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያ ከ29 ሃገራት የተውጣጡ አንድ ሚሊየን የሚጠጉ ስደተኞችን ተቀብላ የሰብዓዊ ድጋፍ አገልግሎት በመስጠት ከአፍሪካ በቀዳሚነት ትጠቀሳለች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.