Fana: At a Speed of Life!

ለ36 ዓመታት ባህር ውስጥ በጠርሙስ የተቀመጠው ደብዳቤ

ይህ እድሜ ጠገብ ደብዳቤ በማሳቹስቴት ግዛት ኬብ ኮድ በተሰኘ የባህር ዳርቻ ጆሽዋ ሜንዲስ በተባለ ግለሰብ ነው የተገኘው።

መልዕክቱ እንደ ውሮፓውያኑ አቆጣጠር 1983 ግንቦት 14 ቀን ሜይኒ ጄኒይ ብሮውን በተባለች የ11 ዓመት ታዳጊ የተፃፈ መሆኑ ተመላክቷል።

መልዕክቱን ያገኘው ሜንዲስ እና አባቱ የጸሃፊዋን አድራሻ  ለማግኘት ሙከራ ሲያደርጉ ቢቆዩም ደብዳቤው ላይ ከፖስታ ሳጥን ቁጥር በስተቀር ምንም አይነት አድራሻ ባለመቀመጡ ምክንያት አላማቸው ሳይሳካ ቆይቷል።

አሁን ላይም ባንጎር ዴይሊ ኒውስ  የተሰኘው የዜና ወኪል በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ባሰፈረው መልዕክት፥ የዚህ ዕድሜ ጠገብ ደብዳቤ ባለቤት መገኘቷን አብስሯል።

ምንጭ፡-www.upi.com

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.