Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል የዘንድሮውን የብሔረ ብሄረሰቦች ቀን ለማክበር በቂ ዝግጅት ማድርጉን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ክልል የዘንድሮውን የብሔር ብሄረሰቦች ቀን ለማክበር በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል።

በዓሉን ለማክበር የተደረገውን ቅድመ ዝግጅት አስመልክቶ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ በዛሬው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው በዓሉ ያለምንም ችግር በሰላም እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

የክልሉ መንግስት ከክልል፣ ከአዲስ አበባ እና ከፌደራል የፀጥታ አካላት ጋር የጋራ እቅድ በማውጣት እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

በዓሉ በልዩነት ውስጥ ያለው አንድነት የሚጎላበት እና ከምንጊዜውም በላይ የእርስ በርስ ግንኙነት የሚጠናከርበት ነው ብለዋል።

በዓሉ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው ነው ያሉት አፈ ጉባዔዋ፥ የእርስ በእርስ የባህል፣ ቋንቋን እና እሴትን ለማጎልበት ፋይዳው የጎላ መሆኑን አብራርተዋል።

በተለይ የኢኮኖሚ ትስስርን ለማሳደግ በዘንድሮው በዓል በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች አውደ ርዕይ እየተካሄደ መሆኑን አንስተዋል።

ለ14ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ ህዳር 29 ቀን በሚከበረው በዚህ በዓል ላይ ከ30 እስከ 35 ሺህ ተሳታፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በተመሳሳይ የትግራይ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ሩፋኤል ሽፋረ፥ የዘንድሮውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በክልል ደረጃ በድምቀት ለማክበር ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።

 

በአዳነች አበበ

You might also like
Comments
Loading...