Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ ህንድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ገበያ ትስስር በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 29 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ትስስሩ የኢትዮጵያና የህንድ የንግድና የፈጠራ ስራ ባለሙያዎች የሽርክና ውል በመፍጠር በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲሰሩ ለማድረግ የተዘጋጀ ነው።

በህንድ በኩል በሀገሪቱ ወደ ስራ የገቡና ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረጉ ያሉ ተቋማትና ግለሰቦች ስራዎቻውን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ማስተዋወቅ ጀምረዋል።

በኢትዮጵያ በኩል 98 የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ፈጠራዎች የተመረጡ ሲሆን፥ ከህንድ የፈጠራ ስራዎችና ባለሙያዎች ጋር ጥምረት ለመፍጠር የሚያችስላቸውን መረጣ እያደረጉ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ በህንድ የለሙና ስራ ላይ ውለው ውጤት ያመጡ ቴክኖሎጂዎችን ለኢትዮጵያ ተስማሚ በሆነ መልኩ ስራ ላይ ማዋል ለተጀመረው የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ አስተዋፅኦ ያደርጋል ብለዋል።

ለስራ እድል ፈጠራና ለቴክኖሎጂ የእውቀት ሽግግር አይነተኛ ሚና ይጫወታልም ነው ያሉት።

በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኑራንግ ስትራቫስታቫ በበኩላቸው፥ ፕሮግራሙ የሃገራቱን ግንኙነት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ለማጠናከር እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

መድረኩ ሳምንቱን ሙሉ የሚቆይ ሲሆን፥ ተቀራራቢ የቴክሎጂና የፈጠራ ስራ ያላቸው በጋራ እንዲሰሩ የመረጣና የማገናኘት ስራ እንደሚከናወን ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.