Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲሷ የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌይን የፊታችን አርብ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ኢትዮጵያ ይገባሉ።

ጉብኝቱ ከአውሮፓ ውጭ ባሉ ሀገራት በአፍሪካ የሚያደርጉት የመጀመሪያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት መሆኑ ተገልጿል።

በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታም የ2019 የኖቬል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ከሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር በተለያዩ ጉዳዩች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚህ ባለፈም ከኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

እንዲሁም ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማህመት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክሩ ይሆናል።

You might also like
Comments
Loading...