Fana: At a Speed of Life!

ስምንተኛው የአፍሪካ የህዋ ሳይንስና ቴክኖሎጂ አመራርነት መድረክ እየተካሄደ ነው  

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 22 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ስምንተኛው የአፍሪካ የህዋ ሳይንስና ቴክኖሎጂ አመራርነት መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

መድረኩ የህዋ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ጥቅምን ለፖለቲካ መሪዎች፣ ለውሳኔ ሰጭዎች፣ ለተመራማሪዎች፣ ለወጣቶችና ለሴቶች ማሳወቅ፣ በአፍሪካ በህዋ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያለውን ችግር በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ፣ የአፍሪካ ሀገራት በህዋ ሳይንስ ቴክኖሎጂ በጥምረት እንዲሰሩ ማነሳሳትን አላማው ያደረገ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ፥ የአፍሪካ ሀገራት የበጀታቸውን 0 ነጥብ 005 ከመቶ ለዘርፉ እንዲያውሉ የሚጠይቀውን የእስቴዛ ስምምነት እንዲተገብሩ ጠይቀዋል።

የእስቴዛ ስምምነት የአፍሪካ ሀገራት ከሀገራዊ ጥቅል ገቢያቸው ውስጥ ከ100 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ውስጥ 5 ዶላሩን ለህዋ ሳይንስ እንዲያውሉት የሚጠይቅ ነው።

በመድረኩ የህዋ ሳንይንስ ቴክሎጂን በማሳደግና ከዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን የአፍሪካ ሀገራት በትብብር መስራት እንዳለባቸው ተነስቷል።

በ8ኛው የአፍሪካ የህዋ ሳይንስና ቴክኖሎጂ አመራርነት መድረክ ላይ ከአሜሪካ፣ ቻይና፣ ፈረንሳይና ጀርመንን ጨምሮ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ የዘርፉ አመራሮችና ምሁራን እየተሳተፉ ይገኛል።

አሜሪካ፣ ሩሲያ፣ ፈረንሳይ እና ቻይና የበጀታቸውን ከ0 ነጥብ 1 እስከ 0 ነጥብ 23 በመቶ ለህዋ ሳይንስ እንደሚያውሉት ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

 

 

You might also like
Comments
Loading...