Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ ጃፓንን አስጠነቀቀች

አዲስ አበባ፣ህዳር 22 ፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ ጃፓንን ማስጠንቀቋ ተሰምቷል።

ሰሜን ኮሪያ ባሳለፍነው ሀሙስ መጠናቸው በውል ያልታወቁ ሁለት ተወንጫፊ ሚሳኤሎችን ወደ ጃፓን ባህር ማስወንጨፏ ተነግሯል።

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፥ ሰሜን ኮሪያ በተደጋጋሚ የምታደርገውን የሚሳኤል ሙከራ ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ሲሉ አውግዘዋል።

የሰሜን ኮሪያ የሚሳኤል ሙከራ ለጃፓን ብቻ ሳይሆን ለመላው ዓለም ስጋት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ሀገሪቱ ከዚህ ድርጊቷ እንድትቆጠብም አሳስበዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ የሰጡትን አስተያየት ተከትሎም ሰሜን ኮሪያ ለጃፓን ከባድ ማስጠንቀቂያ ማስተላለፏ ተሰምቷል።

ፒዮንግያንግ የሚሳኤል ሙከራ አለማድረጓን ገልጻ በወቅቱ መጠኑ ተለቅ ሮኬት ማስወንጨፏን ግን አምናለች።

ይሁን እንጅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ፒዮንግያንግ ሚሳኤል አስወንጭፋለች በሚል የሚያሰሙት ተቃውሞ ከአንድ ትልቅ ፖለቲከኛ የማይጠበቅ ተራ አሉባልታ ነው ስትል አጣጥላለች።

ሺንዞ አቤ የሚሳኤልንና የሮኬትን ልዩነት የማያውቁ ከሆነም በቅርቡ እውነተኛውን ሚሳኤል በሀገራቸው ላይ ሞክረን እናሳያቸው ይሆናል ስትልም አስጠንቅቃለች።

ምንጭ ፦ቢቢሲ

You might also like
Comments
Loading...