Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፂዮን አዋሽ የብረታ ብረት ማምረቻ ፋብሪካን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 4፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል መቐለ የሚገኘውን አዋሽ የብረታ ብረት ማምረቻ ፋብሪካን በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ዶክተር ደብረፂዮንን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ የስራ ሃላፊዎች እና የአከባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

በዚህ ወቅትም ዶክተር ደብረጺዮን ፋብሪካው ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ብረታ ብረቶችን ማምረት በመጀመሩ መደሰታቸውን ገልጸዋል።

ይህም በክልሉ የሚሰሩ የግንባታ ስራዎችን በጥራት እና በተገቢው ጊዜ ለማከናወን ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑን ነው የተናገሩት።

ፋብሪካው በአሁኑ ወቅት ለ500 ዜጎች የስራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን ፥በቀጣይም ከ2 ሺህ 5ዐ0 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

በተመሳሳይ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጺዮን በቅርቡ የእሳት አደጋ ተከስቶበት የነበረው የቮለሲቲ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካንም ጎብኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.