Fana: At a Speed of Life!

ሃገራዊ እሴቶችን ማሳደግ እና ለትዉልዱ ማስተዋወቅ ይገባል- ምሁራን

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)ሃገራዊ እሴቶችን ማሳደግ እና ለትውልዱ ማስተዋወቅ እንደሚገባ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የዘርፉ ምሁራን ተናገሩ፡፡

የታሪክና ባህል ተመራማሪ የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር አህመድ ዘካሪያ በዘመናት የዳበሩ ሃገራዊ እሴቶችን ለማሳደግ ጠንካራ ስራዎች እንደሚጠበቁ ገልፀዋል፡፡

በተለይም ደግሞ የእርቅና ሽምግልና ስርአቶች ለሰላም ካላቸው ፋይዳ አንጻር ተገቢው ትኩረት ተስጥቷቸው ሊተዋወቁ እና በአግባቡ ጥቅም ላይ ሊውሉ እንደሚገባም ነው የተነገሩት፡፡

የሃገር በቀል እውቀቶች ተመራማሪ አቶ አብዱል ፈታህ አብደላህ በበኩላቸዉ ÷ ሃገራዊ እሴቶች ላይ በቂ ጥናትና ምርምር ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡

አሁን ላይ ቸል የተባሉ እና የቀደምት አባትና እናቶች ያቆዩዋቸውን ባህላዊ ትውፊቶች እንደቀደመው ጊዜ ለሰላምና አብሮነት አስተዋጽኦ ያበረክቱ ዘንድ መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡

ምሁራኑ ዘመናዊውን የህግ ስርአት ነገሮችን ከስር መርምሮ መፍትሄ ሲያስቀምጥ ከቆየው ሃገር በቀል እሴቶች ጋር ማስታረቅ ይገባልም ነው ያሉት ፡፡

የሃገር በቀል የእርቅና ሽምግልና ስርአቶች ካላቸዉ ፍልስፍናና ችግሮችን በጥበብ የመፍታት ብሂል አንጻር ትኩረት ተስጥቷቸው ሊበለጽጉና ሊተዋወቁ እንደሚገባም ተመላክቷል ፡፡

በአወል አበራ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.