Fana: At a Speed of Life!

35 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ዳያስፖራዎች የንግድና ኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደዋል

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 7 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ 35 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ከ1 ሺህ 32 በላይ ዳያስፖራዎች የንግድና ኢንቨስትመንት ፈቃድ መውሰዳቸውን አስታወቀ።

ኤጀንሲው የዳያስፖራውን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ልማት ተሳትፎ ይበልጥ ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

በኤጀንሲው የዳያስፖራ ተሳትፎ ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ አውላቸው ማስሬ፥ በተያዘው ዓመት በርካታ ዳያስፖራዎች በንግድ፣ ኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ዘርፎች የጎላ ተሳትፎ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

ዳያስፖራዎቹ በእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ጉልህ አስተዋጾ እንደነበራቸውም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

በበጀት አመቱ ሩብ ዓመትም ከ1 ሺህ 32 በላይ ዳያስፖራዎች የንግድና ኢንቨስትመንት ፈቃድ መውሰዳቸውንም አስረድተዋል።

በዚህም 35 ቢሊየን ብር መነሻ ካፒታል እንዳስመዘገቡ መናገራቸውን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከ4 ሺህ በላይ ዳያስፖራዎች በተለያዩ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ የሂሳብ ቁጥር በመክፈት ከ7 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር በላይ መቆጠባቸውንም ጠቅሰዋል።

 

 

You might also like
Comments
Loading...