Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅ ተጓዦች ምዝገባ መጀመሩን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ግንቦት 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅ ምዝገባ መጀመሩን አስታወቀ።
በዚህም መሰረት የ2014 ዓ.ም የሐጅ ተጓዦች አጠቃላይ አገልግሎት ዋጋ 83 ሺህ 500 ብር መሆኑን ምክር ቤቱ ያወጣው የዋጋ ዝርዝር ያመለክታል።
ምክር ቤቱ የዋጋ ዝርዝሩን እና ብር የሚገባባቸው የባንክ እና ቁጥሮች ይፋ ያደረገ ሲሆን ሀጃጁ ባንክ ያስገባበትን ደረሰኝ ፎቶ ኮፒ አድርጎ በመያዝ ዋናውን ይዞ መምጣት እንደሚጠበቅበትም ነው ያስታወቀው።
የሐጅ ተጓዦች ሊያሟሉ የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች፦
1. ለሐጅ የሚሄደው ግለሰብ ከ65 ዓመት በታች የሆነ
2.የኮቪድ 19 ክትባት የወሰደ እና የማረጋገጫ ወረቀቱን የያዘ
3.የታደሰ ፓስፖርት ያለው፤ ፓስፓርት የሌለውና ጊዜው ያለቀ ከሆነ ወደ ጦር ሃይሎች ሆላንድ ኤምባሲ አጠገብ ዋናው ቢሮ በመምጣት ሂደቱን ማፋጠን ይችላል።
4.ባልና ሚስት አብረው የሚሄዱ ከሆነ የጋብቻ ማረጋገጫ ያስፈልጋል። ግዴታ ነው!
5. ልክ የዛሬ ወር በረራ ስለሚጀመር ቶሎ በመመዝገብ ሂደቱን
የተቀላጠፈ ማድረግ እንደሚቻል ምክር ቤቱ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.