Fana: At a Speed of Life!

ፈረንሳይ ለዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ወታደራዊ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቀች

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳይ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ታጣቂዎችን ለመዋጋት ለምታደርገው ጥረት ወታደራዊ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቀች።

ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በምስራቃዊ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ታጣቂዎችን ለመዋጋት ለሚደረገው ጥረት ሃገራቸው ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል።

ማክሮን ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ሺሴኬዲ ጋር በፓሪስ ባደረጉት ውይይት ፈረንሳይ ድጋፍ እንደምታደርግ ተናግረዋል።

በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃ ባይሰጡም ድጋፉ ወታደራዊ ስልጠና እና በደህንነት ዘርፍ ላይ ያተኮረ እንደሚሆን ፍንጭ ሰጥተዋል።

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል ከአይ ኤስ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ታጣቂ ቡድኖች ተደጋጋሚ ጥቃት ይፈጽማሉ።

ይህን ተከትሎም የሃገሪቱ ጦር ከሰሞኑ በታጣቂዎች ላይ የአፀፋ እርምጃ እየወሰደ ነው።

 

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ

 

You might also like
Comments
Loading...