Fana: At a Speed of Life!

ጤና ላይ የሚሰሩ የኤሌክትሮኒክስ ሲስተም መረጃ የሚሰጥ የጥሪ ማዕከል እና የምርምርና የልህቀት ማዕከል ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ተዛማጅ የሆኑ መረጃዎች ማከማቻ፣ የስልጠና ማዕከል፣ የሶፍትዌር ልማት፣ ጤና ላይ የሚሰሩ የኤሌክትሮኒክስ ሲስተም ላይ መረጃ የሚሰጥ የ24 ሰዓት የጥሪ ማዕከል እና የምርምርና የልህቀት ማዕከል ተመረቀ።

ማዕቀከሉ በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የራስ አበበ አረጋይ መኖርያ ቤት የተገነባ ነው።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን እንዳስታወቁት ማዕከሉ በጤና ሚኒስቴር እና አጋር ድርጅቶች ትብብር የተሰራ ነው።

ማዕከሉ በቅርቡ ስራ እንደሚጀምርም ተገልጿል።

 

You might also like
Comments
Loading...