Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ ከሜሊንዳ ጌትስ ጋር ተወያዩ  

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ሊቀ መናብርት አንዷ ከሆኑት ሜሊንዳ ጌትስ ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸው ፋውንዴሽኑ የመንግሥት ዐበይት የትኩረት መስኮች ላይ አስተዋጽኦ በሚያደርግባቸው መንገዶች ላይ መክረዋል።

ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ኢትዮጵያ የግብርና ምርታማነቷ እንዲጨምር እና ሰፊ የጤና ሽፋን እንዲኖራት ለበርካታ ዓመታት ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like
Comments
Loading...