Fana: At a Speed of Life!

ጉግል በአንድሮይድ ስልኮቹ ላይ ስህተት ለሚያገኝ ሰው የሚከፍለውን ገንዘብ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጉግል በአንድሮይድ ስልኮቹ ላይ ስህተት ለሚያገኝ ሰው የሚከፍለውን ገንዘብ ከ200 ሺህ ዶላር ወደ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ማሳደጉን አስታወቀ፡፡

ጉግል በአንድሮይድ ምርቶቹ ላይ በተገጠመው ካሜራ ላይ ከደህንነት ጥበቃ ጋር የተያያዘ ክፍተት ለሚጠቁም ሰው  ላገኘ ሰው ነው ገንዘቡን እንደሚያበረክት ያስታውቀው።

ኩባንያውም ከፈረንጆቹ 2015 ጀምሮ ለደህንነት ጥናት ከ4 ሚሊየን ዶላር በላይ ክፍያ መፈፀሙን ነው ያስተወቀው፡፡

ጉግል ሽልማቱን የሚያበርክተው ከቲታም ኤም  የደህንነት ቺፕ ወይም  የኦፕሬትን ስርዓቱን ከጥቃት የሚከላከለው  የስልክ ክፍል ስህተት ካወቀና ሌሎች ተጨማሪ መስፈርቶችን ከሟላ ነው ተብሏል፡፡

ፌስቤክ ፣ ቡዝፌድ ፣ አፕል እና ሳምሰንግም ለደህንነት ጋር የተያያዡ ችግሮችን ለሚያሳውቃቸው አካል ሽልማት እንደሚያበረክቱ  ተነግሯል፡፡

ክፍተቶች ከተጠቆሙ በኋላም  ምርቶቹን ላይ ማስተካከለያ እንደሚደረግም ድርጅቶቹ ተናግረዋል።

አንዳንድ የፀጥታ ባለሙያዎች፤ የስልክ ምርቶች ላይ ያሉ ክፍተቶችን ማጋለጥ መረጃው በወንጀለኞች እጅ እንዲገባ መንገድ ይከፍታል የሚል ስጋት አላቸው።

ሆኖም ኩባንያዎቹ ሽልማቱ ሰዎች የሚያገኞቸውን ችግሮች ሲያሳዉቁ የታዩትን ክፍተቶች ለማስተካከል እንደሚያስችል ይገልፃሉ፡፡

 

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like
Comments
Loading...