Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል በ2011 በጀት አመት 230 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሄራዊ ባንክ ማቅረብ መቻሉን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል በ2011 በጀት አመት 230 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሄራዊ ባንክ ማቅረብ መቻሉን የደቡብ ክልል ውሀ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ አስታወቀ

የደቡብ ክልል ውሀ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ እንደገለፁት÷ በ2012 በጀት አመት በክልሉ ህገ ወጥ የወርቅ ንግድና ዝውውርን በመከላከል ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

ህገ ወጥ የወርቅ ንግድና ዝውውርን በመከላከል ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራም ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የወርቅ ማዕድን በሚመረትባቸው አካባቢዎች የመሠረተ ልማት አለመሟላት ፣የፀጥታ ችግር፣ ህገ ወጥ የወርቅ ንግድ እና ዝውውር ከዘርፉ ለሚገኘው ገቢ መቀነስ በምክንያትነት የሚጠቀሱ መሆኑን አቶ አንተነህ አብራርተዋል፡፡

በተያዘው በጀት አመት ከወርቅ ማዕድን ምርት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ከፌደራል ጀምሮ በየደረጃው ካሉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር በዘርፉ የሚስተዋለውን ውስንነት ለመቅረፍ እንደሚሰራ ከክልልመንግስት ኮሙኒኬሽ ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like
Comments
Loading...