Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ 125 ሰልጣኞችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዳማ ከተማ የሚገኘው የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ በተለያዩ የሙያው መስኮች ያሰለጠናቸውን 125 ባለሙያዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

ኮሌጁ በሁለተኛ ዙር ያሰለጠናቸውን የዘርፉ ባለሙያዎች ነው በዲፕሎማ ማዕረግ ያስመረቀው።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የኦሮሚያ የፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቀነአ ያደታ፣ የተለያዩ ክልሉ አመራሮችና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

ተመራቂዎች የህብረተሠቡን ሰላምና ህንነት ለማስጠበቅ የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ ቀርቧል።

You might also like
Comments
Loading...