Fana: At a Speed of Life!

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ “ጋሻ“ የተሰኘ ጸረ-ቫይረስ አበለፀገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) “ጋሻ“ የተሰኘ ጸረ-ቫይረስ ማበልጸጉን አስታውቋል።

ጸረ ቫይረሱ በኔትወርክ እና በኮምፒዩተሮች ውስጥ ባሉ መተግበሪያዎች የሚመጡ ጥቃቶችን ለመቆጣጠር የሚያስችል መሆኑ ነው የተገለጸው።

የኤጀንሲው የሳይበር እድገት ዳይሬክቶሬት የኢንፎርሜሽን ደህንነት ባለሙያ አቶ ናምሩድ ከሰተብራሃን፥ፀረ ቫይረሱ በሀገራችን ላይ የሚቃጡ የቫይረስ ዓይነቶችን ታሳቢ በማድረግ እና ዓለም ላይ አሉ የተባሉ ዋነኛ የቫይረስ ዓይነቶችን እንዲከላከል ተስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል።

“ጋሻ” አንድን የቫይረስ ዓይነት ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የቫይረስ ዓይነቶችን መከላከል እንዲችል ታሳቢ ተደርጎ የተሰራ መሆኑን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ጸረ-ቫይተሱ በሀገር ውስጥ መሠራቱ የራስ አቅምን ከማጎልበት ባለፈ ለደህንነት ማስጠበቂያ ተብለው ከውጭ ሀገር የሚገቡ ምርቶች በራሳቸው የደህንነት ሥጋት የሚሆኑበትን አጋጣሚ የሚያስቀር መሆኑ ተመላክቷል።

ስለሆነም መተግበሪያው አስፈላጊውን የብቃት ፍተሻ ሂደት ካጠናቀቀ በኋላ ለተጠቃሚዎች የሚተላለፍበት ሁኔታ እንደሚፈጠር አቶ ናምሩድ ተናግረዋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በአዋጅ ከተሰጡት ሥልጣንና ኃላፊነቶች መካከል የኢንፎርሜሽን መሠረተ ልማቶችን እና ሥርዓቶችን ማበልፀግና መዘርጋት ተጠቃሾች ናቸው።

You might also like
Comments
Loading...