Fana: At a Speed of Life!

የአሜሪካ ባለሀብቶች ልዑካን ቡድን በዓርባ ምንጭ ከተማጉብኝት እያደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካ ባለሀብቶች ልዑካን ቡድን በዓርባ ምንጭ ከተማ ጉብኝት እያደረገ ነው።

“ስማርት ቪሌጅ” የሚል መጠሪያ ያለው የአሜሪካ ባለሀብቶች ልዑካን ቡድን በትናንትናው እለት ነው አርባ ምንጭ ከተማ የገባው።

ከልዑካን ቡድኑ ጋርም በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ አርባ ምንጭ ከተማ ገብተዋል።

ልዑካን ቡድኑ ዓርባ ምንጭ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የጋሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ፣ የዓርባ ምንጭ ከተማ ከንቲባ አቶ ሰብስቤ ቡናቤ፣ ከፍተኛ አመራሮችና የሀገር ሽማግሌዎች አቀባበል አድርገውለታል።

የጋሞ ዞን አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አሰግድ ተረፈ እንደገለጹት፥ ቡድኑ በከተማዋ የሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ያደርጋል።

ቡድኑ የድርጅቱን መስራችና ፕሬዚዳንት እንዳካተተና በቆይታውም በከተማዋ በመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ዘርፍ መሰማራት በሚቻልበት መንገድ ላይ ይመክራል ብለዋል።

ዓርባ ምንጭ የኢኮ ቱሪዝም ልማት ተመራጭ አካባቢ መሆኑ ይታወቃል።

 

ምንጭ፦ ኢዜአ

You might also like
Comments
Loading...