Fana: At a Speed of Life!

የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ግሪክ ገብተዋል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2012 (ኤፍ .ቢ.ሲ) የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በዛሬው ዕለት ግሪክ አቴንስ ገብተዋል።

ሺ ጂንፒንግ በግሪክ የሚያድርጉት የስራ ጉብኝትም የቻይና ፕሬዚዳንት ከ11 ዓመታት በኋላ ሀገሪቱን ሲጎብኝ የመጀመሪያ ያደርገዋል።

ፕሬዚዳንቱ በግሪክ በሚኖራቻ ቆይታም ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ፕሮኮፒስ ፓቭሎፖውሎስ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ኪሪያኮስ ሚቲሶታኪስ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በዚህም በሀገራቱ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙት ቀጣይነት ባለው መልኩ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የሚወያዩ መሆኑ ተነግሯል።

ቻይና እና ግሪክ የጥንታዊ ሰልጣኔ ባለቤት መሆናቸውን ያስታወሱት ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ፥ ሀገራቱ በመካከላቸው ያለውን ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር በቅንጅት መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

ሀገራቱ ለዓለም ሰላም፣ መረጋጋት፣ ልማት እና ብልፅግና የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ለማበርከትም በዋና ዋና ዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ መስራት እንደሚገባቸውም ተመላክቷል።

ምንጭ፦ሲ ጂ ቲ ኤን

You might also like
Comments
Loading...