Fana: At a Speed of Life!

ከአዞ መንጋጋ ጓደኛዋን የታደገችው የ11 ዓመቷ ታዳጊ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጓደኛዋን ህይወት ለመታደግ ከአዞ ጋር ትንቅንቅ ያደርገችው ርብቃ የተባለች የ11 ዓመትዋ ታዳጊ ብዙዎቹን እያነጋገረች ነው ፡፡

ርብቃ እና ጓደኟዋ በመኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ ከሚገኝ ወንዝ ዋኝተው ሲመለሱ÷ ከውሃ ውስጥ ጩኸት ይሰማሉ፡፡

የ11 ዓመቷ ርብቃም ጩኸቱ ወዳለበት ስትመለከት የ9ኝ ዓመቷ ጓደኛዋ ላቶያ ሙዋኒ በአዞ እየተጎተተኝ መሆኑን ተመለከተች፡፡

በሁኔታው  ከፍተኛ ድንጋጤ የተሰማት ርብቃ ጓደኛዋን ለመታደግ ወደ ውሃው ዘላ ገብታለች፡፡

በአካባቢው አብረዋቸው ከነበሩት ጓደኞቻቸው የተወሰኑት  በድንጋጤ ባሉበት ሲቆሙ የተወሰኑት ደግሞ ከአካባቢው ተሰውረዋል፤ ያን ማድረግ ያልቻለችው ርብቃ ወደ ውሃው በመግባት ከአዞው ጋር ትንቅንቅ አድርጋለች፡፡

ወደ ወንዙ ዘላ የገባቸው ርብቃ የዓዞ ጭንቅላት ላይ በመውጣት በባዷ እጇ ስትመታው እደነበረ በመግለፅ በጣቶቿ የአዞው ዓይን  ላይ ጥቃት ስትፈፅም አዞ ጓደኟን እንደለቀቃት ተናግራለች፡፡

አዞው ጓደኛዋን ከለቀቃት በኋላ ጉዳት ለማድረስ  እንዳልሞከረ የተናገረችው ርብቃ በዋና ጓደኞቻቸው ወደ ሚገኙበት ስፋራ ማቅናታቸውን ገልፃለች፡፡

ምንጭ፡-ኦዲቲ ሴንተራል

በፌቨን ቢሻው

You might also like
Comments
Loading...