Fana: At a Speed of Life!

እስራኤል ተመራማሪዎች ካርበንዳይ ኦክሳይድ ብቻ የሚመገብ ባክቴሪያ አበለጸጉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራኤል ተመራማሪዎች ካርበንዳይ ኦክሳይድ ብቻ የሚመገብ ባካቴሪያ ማራባት መቻላቸውን ይፋ አድርገዋል።

ተመራማሪዎቹ ባክቴሪያውን ለማበልጸግ “ኢ-ኮሊ” የተሰኘ ፕሮግራም የተጠቀሙ ሲሆን፥ ምርምሩን ለማጠናቀቅም ከ10 ዓመት በላይ እንደወሰደባቸው ገልጸዋል።

ባክቴሪያው ለምግብነት ስኳርን የሚጠቀም ሲሆን፥ ምግቡን ለማዘጋጀትም በከባቢ አየር የሚገኘውን ካርበንዳይ ኦክሳይድ ብቻ ይጠቀማል።

ይህም በአሁኑ ወቅት ዓለም ላይ በሚለቀቀው የተበከለ ጋዝ ምክንያት የሚከሰተውን የከባቢ አየር ሙቀት ለመቀነስ እንደሚያስችል ታምኖበታል።

ከዚህ ባለፈም ባክቴሪያው የተሰራበት ፕሮግራም ዓለም ላይ እየተስተዋለ ያለውን የሙቀት ችግር ለመቀነስ የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን ለመፈብረክ ፍንጭ የሚሰጥ ነው ተብሏል።

ተመራማሪዎቹ በቀጣይ ካርበንዳይ ኦክሳይድ ብቻ የሚመገበውን ባክቴሪያ ዘረ መል በአይነትም ሆነ በቁጥር ለማሳደግ ከሚመለከተው አካል ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ሺንዋ

You might also like
Comments
Loading...