Fana: At a Speed of Life!

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ 98 የቱርክ ሽጉጥ ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ በሳንጃ ጉምሩክ ቅርንጫፍ መቆጣጠርያ ጣቢያ 98 የቱርክ ሽጉጥ ተያዘ፡፡
የወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ረዳት ኢንስፔክተር ከፋለ አለሙ እንደገለፁት ህገ ወጥ ሽጉጡ መነሻውን ከምዕራብ አርማጭሆ ከአብራጅራ ከተማ -ጎንደር ከተማ ባደረገ ባጃጅ ተሸከርካሪ ወደ ጎንደር ለማለፍ ሲሞክር በተደረገ ፍተሻ የተያዘ ነው፡፡
ሹፌሩም እንዳመለጠ ከታች አርማጨሆ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በኮንትሮባንድ እንቅስቃሴና ህገ ወጥ ንግድ ላይ ጥብቅ ፍተሸ እያደረጉ መሆናቸውን የገለፁት እንስፔክተሩ ህገ ወጦች ከእንዲህ አይነት ብልሹ ተግባራቸው እንዲታቀቡና ህብረተሰቡ ጥቆማ እንዲያደረስ መልዕክት አስተላልፈዋል ።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.