Fana: At a Speed of Life!

ሰርገኞችን ግብር የምታስከፍለዋ መንደር

አዲስ አበባ፣ህዳር 5፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በናይጀሪያ ኬራ  የተሰኘቸው ግዛት አስተዳዳሪ አዶ ሳኢድ ሰርገኞች  ግብር እንዲከፍሉ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው ተሰምቷል።

በዚህ መሰረትም ማንኛውም በሰፈሪቱ ሶስት ጉልቻ ለመመስረት ሰርግ የሚደግስ ሰርገኛ 137 ሺህ ናይራ ግብር መክፈል ይጠበቅበታል።

ይህም ከዚህ በፊት ሙሽራው ለሙሽሪት ቤተሰቦች የሚያቀርበውን የስጦታ ዕቅ፣ገነዘብ ወይም ጥሎሽ ገ የሚያስቀር መሆኑ  ተነግሯል።

በሙሽሮች ላይ የሚጣለው ቀረጥ ውሳኔ የተላለፈውም ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ምክክር ተደርጎበት መሆኑን ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል።

በአንፃሩ ድርጊቱ በሰፈሪቱ የሚኖሩ ሰዎችን በእጅጉ ያስቆጣ መሆኑ በዘገባው ተመላክቷል።

እንደ ነዋሪዎቹ ገለፃ  በሰርገኞች ላይ እንዲጣል የተወሰነው አዲሱ ግብር ከአካባቢው ማህበረሰብ ባህልና ወግ ያፈነገጠ ነው።

በተለይም ሙሽራው ለሙሽሪት ቤተሰብ የሚሰጠው ስጦታ ወይም ጥሎሽ እንዲቀር መደረጉ የአካባቢውን ማህበረሰብ   የቀደመ ባህል የሚሸረሽር መሆኑን ተናግረዋል።

በአዲሱ ግብር  ምክንያትም ባለፉት አራት ወራት በሰፈሪቱ ምንም አይነት ሰርግ ተደግሶ የማያውቅ መሆኑ ነው የተገለጸው።

ምክንያቱንም ትዳር ለመመስረት የሚጋቡ ጥንዶች የተጣለውን ግብር በመቃወም ሌላ አካባቢ ሄደው ማግባት በመጀመራቸው ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ https://www.myjoyonline.com/

You might also like
Comments
Loading...