Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ የቡርቃ ዋዩ እንደኛ ደረጃ ት/ቤትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣2012 (ኤ ፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የአፋን ኦሮሞ ትምህርት ቤት የሆነውን ቡርቃ ዋዩ እንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጎብኝተዋል፡፡

በትምህርት ቤቱ ያለውን የትምህር አሰጣጥ ሂደት የተመለከቱት ኢንጂነር ታከለ ኡማ፥ ከመምህራን እና የተማሪ ወላጆች ጋር ቆይታ አድርገዋል።

የተማሪ ወላጆች በዩኒፎርም ስርጭት ወቅት በትምህርት ቤቱ ስላጋጠመው እጥረት እና ሌሎች ችግሮችን በተመለከተ ለኢንጂነር ታከለ ኡማ ጥያቄ አቅርበዋል።

ኢንጂነር ታከለ በምላሻቸው አስተዳደሩ ይህንን ትምህርት ቤት ጨምሮ በሌሎች ትምህርት ቤቶች በሚነሱ ጥያቄዎች ላይ በአጭር ጊዜ ማስተካከያ እንደሚያደረግ ተናግረዋል።

ጀሞ አካባቢ የሚገኘው የቡርቃ ዋዩ እንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወደስራ የገባው በዚህ ዓመት ሲሆን፥ 5 ሺህ 342 ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ መሆኑን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like
Comments
Loading...