Fana: At a Speed of Life!

ሃንጋሪ 5ኛ ትውልድ ኔትወርክን ለመጀመር ከሁዋዌ ጋር ተስማማች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሃንጋሪ ከቻይናው የቴሌኮሙዩኒኬሽን ኩባንያ ሁዋዌ ጋር 5ኛ ትውልድ (5 ጂ) ኔትዎርክ ግንባታ ዙሪያ በአጋርነት ልትሰራ ነው፡፡

የሃንጋሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፒተር ሲዚጃርቶ በሻንጋይ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ጉባኤ ላይ እንዳሉት፥ ሃንጋሪ ዜግነትን መሰረት አድርጋ ማንኛንም ኩባንያ አታገልም።

በተጨማሪም ከሃንጋሪ ጋር ለመስራት የውስጥ ህግና ደንብን ማክበር ብቻ በቂ እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡

በቀጣይም ሁዋዌ የ5ኛ ትውልድ ኔትዎርክ ግንባታን ከቮዳፎን እና ዲውቼ ቴሌኮም ጋር በጋራ ይሰራል ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡

አክለውም ሃንጋሪ ከትንሽም ይሁን ከመካከለኛ ድርጅቶች ጋር በንግድ ዙሪያ ለመስራት በሯ ክፍት ነው ብለዋል፡፡

በተለይም አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ይዘው ለሚመጡ ድርጅቶች ግብር እንደሚቀንሱና ድጋፍ እንደሚደረግላቸውም ገልጸዋል።

ምንጭ፡- ሲ ጂ ቲ ኤን

You might also like
Comments
Loading...