Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከዓለም አቀፍ ሜትሪዎሎጂ ድርጅት ዋና ፀሃፊ ፔቴሪ ታላስ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በአለም አቀፍ የሜትሪዎሎጂ ድርጅት ዋና ፀሃፊ ፔቴሪ ታላስ የተመራ ልኡካን ቡድንን በብሄራዊ ቤተ መንግስት ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
 
በዚህ ወቅትም የድርጅት ዋና ፀሃፊ ፔቴሪ ፔቴሪ ታላስ የዓለም አቀፍ ሜትሪዎሎጂ ድርጅት የአፍሪካ ፅህፈት ቤቱን በአዲስ አበባ ከተማ መክፈቱን አስመልክተው ለፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ገለጻ አድርገዋል።
 
እንደ ዋና ፀሃፊው ገለፃ የድርጅቱ ፅህፈት ቤት በአዲስ አበባ እንዲከፈት የተወሰነው በአከባቢው የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት የሚያስከትልባቸው ብዙ አፍሪካውያን እንደሚኖሩ ታሳቢ በማድረግ ነው።
 
በተጨማሪም ይህ ሁኔታ አፍሪካውያን የአየር ንብረት ለውጥ ስጋቶችን በተመለከተ ያላቸውን ትምህርት ለመውሰድ እና የተሻሉ የአየር ንብረት አገልግሎቶችን ለመስጠት እንደሚያስችል ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
እንዲሁም የብሔራዊ ሜትሪዎሎጂ እና ሃይድሮሎጂ አገልግሎቶችን ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችል መሆኑን ነው ያብራሩት።
 
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በበኩላቸው አዲስ አበባ የድርጅቱ የአፍሪካ ፅህፈት ቤት መቀመጫ ሆና መመረጧን አድንቀዉ ኢትዮጵያ ከድርጅቱ ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላት ገልፀዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.