Fana: At a Speed of Life!

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ “መደመር” መፅሃፍ ምረቃ በሚሌኒየም አዳራሽ ተካሂዷል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተፃፈው “መደመር” መፅሃፍ ምረቃ በሚሌኒየም አዳራሽ ተካሂዷል።

በምረቃው ላይም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሰላም የኖቤል ተሸላሚ በመሆናቸው እንኳን ደስ አላችሁ እንዷን ደስ አለን ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የሰላም የኖቤል ተሸላሚ በመሆን የሀገራችንን ስም በዓለም መድረክ በድጋሚ ስላስጠሩ ምስጋና ይገባቸዋልም ብለዋል።

እንዲሁምከቤተሰባቸው እና ከራሳቸው ካላቸው ጊዜ ቀንሰው ይህንን የመሰለ መፅሃፍ ስላበረከቱልን እናመሰግናለን ብለዋል ኢንጂነር ታከለ በንግግራቸው።

 

የመፅሃፉ ምረቃም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ አዲስ አበባን ጨምሮ በ20 ከተሞች ዛሬ ተከናውኗል።

በዋናነትም በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ጅማ፣ ባህር ዳር፣ ሀዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ ጋምቤላ፣ አሶሳ፣ ጅግጅጋ፣ ሰመራ እና ሀረር ከተሞች የምረቃ ስነ ስርዓቱ ተካሂዷል።

በምረቃ ስነ ስርዓቶቹ ላይም የየከተሞቹ ነዋሪዎች፣ ባለስልጣናት፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች እና ሴቶች ተገኝተዋል።

በየአካባቢው ባህል መሰረት የምረቃ ስነ ስርዓት የሚከናወን ሲሆን፥ ስለ መፅሃፉ አጠቃላይ መረጃም ማብራረሪያ ተሰጥቷል።

መፅሃፉ በአማርኛ ፣በኦርምኛ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋዎች የተዘጋጀ ሲሆን፥ 1 ሚሊየን ቅጂዎችም ታትመዋል።
የኢንግሊዘኛው ቅጂ ግን ከሶስት ወራት በኋላ እንደሚደርስ ተመልክቷል።

የመፅሃፉ ዋጋ 300 ብር ሲሆን፥ ገቢውም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ትምህርት ቤቶችን ለማስገንባት ይውላል ነው የተባለው።

ከሀገር ውስጥ ምረቃ በኋላም በውጭ ሀገራት በአሜሪካ እና ኬንያ በተለይም በዋኝንግተን ዲሲ፣ ሎስ አንጀለስ፣ ሚኒሶታ እና ናይሮቢ የምረቃ ስነ ስርዓቱ የሚከናወን ይሆናል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.