Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ ፈረንሳይ ቢዝነስ ፎረም በፈረንሳይ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮ ፈረንሳይ ቢዝነስ ፎረም በፈረንሳይ ፓሪስ እየተካሄደ ነው።

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በቢዝነስ ፎረሙ የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመክፈቻው ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ምድረ ቀደምት ሃገር፤ የብዝሃነት መኖሪያ እና የኢንቨስትመንት ተመራጭ መዳረሻ መሆኗን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ዘላቂ ልማት እና ሁሉን አቀፍ ዕድገት በፍጥነት ለማረጋገጥ የተለያዩ የማሻሻያ ፕሮግራሞች ተግባራዊ በመደረግ ላይ መሆናቸውንም አንስተዋል።

የኢትዮጵያ እና የፈረንሳይ ትብብር የበለጠ ሊጎለብት የሚችለው በንግድ እና በኢንቨስትመንት ትርጉም ባለው ደረጃ መደገፍ ሲቻል መሆኑንም አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ ለውጭ ባለሃብቶች የተመቸ የኢንቨስትመንት ድባብ ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

በፎረሙ ለተሳተፉ የኢትዮጵያ እና የፈረንሳይ ባለሃብቶች የሁለቱን ሀገራት ትብብር በንግድ እና በኢንቨስትመንት ትስስር እንዲያጠናክሩ ጥሪ ማቅረባቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.