Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት ብሪታኒያ ከህብረቱ የምትወጣበትን ጊዜ አራዘመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአውሮፓ ህብረት ብሪታኒያ ከህብረቱ የምትወጣበትን ጊዜ በሶስት ወራት ማራዘሙ ተሰምቷል።

የአውሮፓ ህብረት መሪዎች የብሪታኒያ እና የህብረቱን ፍቺ እስከ አውሮፓያኑ ጥር 31 ቀን 2020 ሊራዘም በሚችልበት መርህ ላይ ስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል።

የአውሮፓ ህብረት ካውንስል ፕሬዚዳንት ዶናል ታስክ ስምምነቱ በፓርላማው ተቀባይነት አግኝቶ ከፀደቀ ፍቺው ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ ቀደም ብሎ ተፈፃሚነት ሊኖረው እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

ይህ መረጃ የወጣው የብሪታኒያ ፓርላማ ሀገሪቱ በአውሮፓውያኑ ለታህሳስ 12 2019 ለማካሄድ ባቀደችው ምርጫ ዙሪያ ድምጽ ለመስጠት እየተዘጋጀ በላበት ወቅት ነው ተብሏል።

የብሪታኒያ እና የአውሮፓ ህብረት ፍቺ ለሚቀጥለው ሃሙስ ቀነ ገደብ ተይዞለት የነበረ መሆኑን ይታወሳል።

በህብረቱ የብሪታኒያ ፍቺ ጉዳዩች ዙሪያ የብሪታኒያ ፓርላማ አባለቱ ስምምነት ላይ ያለመደረሳቸው ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ጉዳዩን ለሌላ ጌዜ እንዲያራዝሙ የግድ እንዳደረገባቸው ነው የተነገረው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.