Fana: At a Speed of Life!

የህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ብሔራዊ ምክር ቤት 11ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት 11ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።

የኤፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የብሔራዊ ምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ደመቀ መኮንን በጉባኤው ላይ የተሰጡ ጥቆማዎች እና አስተያየቶች ለ2012 እቅድ አፈፃፀም ጠቀሜታው ከፍ ያለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ታሪካዊ የሀገር መገለጫ መሆኑን በመግለጽ በ2012 ዓመተ ምህረት ለፍፃሜው የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ያስፋልጋል ብለዋል፡፡

ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ እትዮጵያአዊያን የተስበስበን ሂሳብ ተገቢውን መንገድ በመሰብሰብ ለታለመለት ዓለማ ማዋል እንደደሚገበው እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለዜጎች ተደራሽ መድረግ እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

ዛሬ በተጀመረው የብሄራዊ ምክር ቤቱ ጉባኤ ላይ የ2011 እቅድ አፋጻጸም እና 2012 እቅድ ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ይገኛል።

የህዝባዊ ተሳትፎ ብሄራዊ ምክር ቤት አባላቱ የታላቁ ህዳሴ ግድብ የተርባይን መጠኑ ለምን ቀነሰ በሚለው ጉዳይ እና ኢትዮጵያ ከግብፅ ለቀረበው ሀሳብ በወሰደችው አቋም ዙሪያ ጥያቄዎችን አነስተው ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።

ግድቡ በደለል እንዳይሞላ ከወዲሁ በጥንቃቄ መስራት እንደሚገባም በውይይቱ ተነስቷል።

በህዝቡ ዘንድ የተቀዛቀዘውን ስሜት እንደገና እንዲነሳሳ ማድረግ እንደሚያስፈለግም በብሔራዊ ምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤ ላይ ከተነሱ ጉዳዮች ተጠቃሽ ነው።

በሲሳይ ጌትነት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.