Fana: At a Speed of Life!

ጎግል የበካይ ጋዞችን ልቀት መጠን መለካት የሚያስችል መሳሪያ ይፋ አድርጓል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጎግል የተሰኘው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ከተማዎች ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቁትን ጋዞች መጠን ለመለካት የሚያስችላቸውን መሳሪያ ይፋ አድርጓል።

መሳሪያው  ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቁ በካይ ጋዞችን መጠን የሚያሳውቀውም  ከትራንስፖርት አገልግሎትና ከህንፃዎች የሚገኙ መረጃዎችን  መሰረት በማድረግ መሆኑ ተገልጿል።

ለዚህም  መሳሪያው የጎግል ካርታን  የሚጠቀም መሆኑ በዘገባው ተመላክቷል።

በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ የሚስተዋለው ከፍተኛ የአየር ንብረት ለውጥ አሳሳቢ መሆኑ ይታወቃል።

መሳሪያው በከተማዎች በየጊዜው የሚለቀቀዉን የበካይ ጋዞች መጠን ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ ችግሩን ለመፍታት የተለያዩ እርምጃዎች እንዲወሰዱ የሚስችል መሆኑ ተገልጿል።

ምንጭ ፦ቢቢሲ

You might also like
Comments
Loading...