Fana: At a Speed of Life!

ጎግልና ፌስቡክ በዓለም አቀፉ የበይነ መረብ ኮንፈረንስ አልተሳተፉም

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 10፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጎግልና ፌስቡክ በዓለም አቀፍ የበይነ መረብ ኮንፈረንስ ላይ አለመሳተፋቸው ታውቋል ።

6ኛው ዓለም አቀፍ የበይነ መረብ ኮንፈረንስ በምስራቅ ቻይና ሁዜን ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

በአሜሪካ እና ቻይና መካከል በተፈጠረው የንግድ ጦርነት ምክንያት በዋሽንግተን የሚገኙ ትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በዘንድሮው ዓለም አቀፍ የበይነ መረብ ኮንፈረንስ ላይ አለመሳተፋቸው ታውቋል።

በዚህ መሰረትም ጎግል፣ ፌስቡክ፣ትዊተር እና አፕል የተሰኙ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በኮንፈረንሱ ያልተሳተፉ ሲሆን፥ ትንሽ ቁጥር ያላቸው የአሜሪካ ቴክኖሎጂ ተቋማት ብቻ መሳተፋቸው ተጠቁሟል።

ጎግል፣ትዊተር እና ፌስቡክ በቻይና አገልግሎት እንዳይሰጡ መታገዳቸው ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም ሁዋዌ የተሠኘው ግዙፍ የቻይና የቴሌኮም ኩባንያ እነዚህን መተግበሪያዎች ሊተኩ የሚችሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ማበልጸጉን አስታውቋል።

ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በሚካሄደው በዚህ ኮንፈረንስ ፥ የተለያዩ አዳዲስ የበይነ መረብ አገልግሎቶች ለደንበኞች ይፋ ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ኮንፈረንሱ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የበይነ መረብ አግልግሎት ሰጪ ድርጀቶችንና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን የሚያመርቱ ኩባንያዎችን ይበልጥ ለማስተሳሰር የሚያስችል መሆኑ ተነግሯል።

ምንጭ ፥ www.scmp.com

You might also like
Comments
Loading...