Fana: At a Speed of Life!

ተመድ በቀጣዩ ወር ለሰራተኞቹ የሚከፍለው ገንዘብ ላይኖረው ይችላል-ጉቴሬዝ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገራት የሚጠበቅባቸውን ክፍያ ለድርጅቱ ካልፈፀሙ በቀጣዩ ወር ለሰራተኞቹ የሚከፍል ገንዘብ ላይኖረው እንደሚችል ዋና ፀሃፊው አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አስጠነቀቁ፡፡

ዋና ፃሃፊው 193 አባላት ባሉት በተመደ ጠቅላላ ጉባኤ የበጀት ኮሚቴ ባደረጉት ንግግር ከባለፈው ጥር ወር ጀምሮ ድርጅቱ የሚያወጣውን ወጪ መቀነስ ባይቻል ኖሮ በቅርቡ የተካሄደውን የመሪዎች ስብሰባ ማስተናገድ አይቻልም ነበር ብለዋል፡፡

ተመድ በአስርት ዓመታት ውስጥ በተያዘው ወር ከፍተኛ የበጀት እጥረት ላይ ይደርሳል ያሉት ዋና ፀሃፊው፥ በዚህም ያለምንም ገንዘብ ወደ ቀጣዩ ወር ሊገባ ይችላልም  ነው ያሉት፡፡

ጉቴሬዝ የድርጅቱ ስራ እና የሚካሄደው ለውጥ አደጋ ላይ ናቸው ሲሉ ድርጅቱ ያጋጠመው የገንዘብ እጥረት አሳሳቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከአባል ሀገራቱ መካከል ከፍተኛውን በጀት የምትሸፍነው አሜሪካ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የ2019 በጀት 22 በመቶውን ትሸፍናለች፡፡

በዚህም ባለፈው ዓመት ከተመድ መደበኛ በጀት 381 ሚሊየን ዶላር የሸፈነችው አሜሪካ ከ2019 የተመድ መደበኛ ወጪ ውስጥ 674 ሚሊየን ዶላሩን እንደምትሸፍን አስታውቃለች፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ

You might also like
Comments
Loading...