Fana: At a Speed of Life!

ጃኮብ ዙማ ፈጽመውታል ከተባለ ሙስና ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 4 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ አፍሪካው የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ነው።

ዙማ በሙስና፣ ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና በድብቅ ከተፈጸሙ ትልልቅ ስምምነቶች ጋር በተያያዙ 16 ክሶች ይቀርብባቸዋል ነው የተባለው።

ግለሰቡ የፈረንሳይ የመከላከያ ቁሳቁሶች አምራች ኩባንያን ጨምሮ ከተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት ኩባንያዎች በርካታ መጠን ያለው ገንዘብ ተቀብለዋል ተብሏል።

ገንዘቡ ደቡብ አፍሪካ ከፈጸመችው የጦር ጀት፣ ቃኝ ጀልባዎች እና የተለያዩ የመከላከያ ቁሳቁሶች ግዥ የተቀበሉት መሆኑም ተገልጿል።

ከዙማ ጋር በሙስናው ወንጀል አብሯቸው ተሳትፏል የተባለው የፈረንሳዩ ቴልስ ግሩፕ ኩባንያ ተወካዮችም ፍርድ ቤት ይቀርባሉ።

ጃኮብ ዙማ ከዚህ ቀደም ከሙስና ጋር በተያያዘ በርካታ ውንጀላዎች ቢቀርቡባቸውም ጠንከር ባለ የፍርድ ሂደት አልተጠየቁም።

ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርቡበታል የተባለው ጉዳይም ዙማ በምክትል ፕሬዚዳንትነት ሃገራቸውን ባገለገሉበት 19 90ዎቹ ከተፈጸመ የመከላከያ ቁሳቁስ ግዥ ጋር የተያያዘ ነው።

ዙማም ሆኑ የፈረንሳዩ ኩባንያ የቀረበባቸውን ውንጀላ አስተባብለዋል።

 

 

ምንጭ፦ አልጀዚራ

You might also like
Comments
Loading...