Fana: At a Speed of Life!

ዶናልድ ትራምፕ ቻይና  ጆ ባይደን ላይ ምርመራ እንድትጀምር ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ዶናልድ ትራምፕ ዋነኛ የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተፎካካሪዎች በሆኑት ጆ ባይደን ላይ ቻይና ምርመራ እንድትጀምር ጠየቁ፡፡

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዚህ ቀደም ከዩኩሬኑ ፕሬዚዳንት ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት በተመሳሳይ በጆ ባይደን እና በልጃቸው ላይ ምርመራ እንዲጀመር ጥያቄ አቅርበው ነበር፡፡

ይህንንም ተከትሎ በዶናልድ ትራምፕ ላይ የሀገሪቱ ህዝብ ተወካዮች ክስ መመስረታቸው የሚታወስ ነው፡፡

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት  ቻይና እና ዩክሬን ዲሞክራቶችን በመወከል በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እየተሳተፉ በሚገኙ ጆ ባይደን እና ልጃቸው ላይ ክስ ሊመሰርቱ ይገባል ብለዋል፡፡

ዲሞክራቶች ዶናልድ ትራምፕ ወታደራዊ ድጋፍ ን በመጠቀም ዩክሬን በጆ ባይደን ላይ ክስ እንድትመሰርት ጫና አሳድረዋል ሲሉ ክስ አቅርበዋል፡፡

ጆ ባይደን ለዶናልድ ትራምፕ በትዊተር ገፃቸው በሰጡት ምላሽ  ዶናልድ ትራምፕ በሰው ሞራል ላይ የሚፈፅሙ ጥቃት ቀልድ ነው ሲሉ አስፍረዋል፡፡

ትራምፕ የቀረበባቸው ክስ ማለትም በኮንገረስ በኩል እርሳቸው ከስልጣን ለማውረግ የሚደረገው ጥረት የወረደ ተግባር ነው አጣጥለዋል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

You might also like
Comments
Loading...