Fana: At a Speed of Life!

ያለፉት 2 ወራት የወጪ ንግድ ገቢ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ69 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ጭማሪ አስመዘገበ

 

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ያለፉት ሁለት ወራት የወጪ ንግድ ገቢ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ69ነጥብ 92 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ጭማሪ አስመዘገበ፡፡

ውጤቱ የተገኘው የተፈጥሮ ሙጫና ዕጣን፣ አበባ፣ የብርዕና አገዳ ዕህሎች፣ ኤሌክትሪክ፣ ጫት፣ የኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓት፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ጨርቃ ጨርቅ መሆኑን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በየጥራጥሬ ሰብሎች፣ አትክልትና ፍራፍሬ እና ቡና ከ75 በመቶ እስከ 99 በመቶ የእቅድ ክንውን ተመዝግቧል ነው የተባለው፡፡

የቅባት እህሎች፣ ታንታለም፣ የቁም እንስሳት፣ ስጋ፣ ባህር ዛፍ፣ ሰም እና ቆዳና የቆዳ ውጤቶችም ከ50በመቶ እስከ 74በመቶ የአቅድ ክንውን መመዝገቡ ተገልጿል፡፡

በወተትና የወተት ተዋጽኦ፣ ቅመማ ቅመም፣ ምግብ መጠጥና ፋርማስዩቲካልስ፣ ወርቅ፣ ማር፣ ሌሎች ማዕድናት፣ የሥጋ ተረፈ ምርት፣ ሻይ ቅጠል፣ ብረታ ብረት እና ዓሣ ምርቶች ከእቅዳቸው ከ50 በመቶ በታች የሆነ የውጭ ምንዛሬ መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like
Comments
Loading...