Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ አርሶ አደሮች ፌዴሬሽን በገላን ከተማ ያስገነባው የዱቄት ፋብሪካ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ አርሶ አደሮች ፌዴሬሽን በገላን ከተማ ያስገነባው የዱቄት ፋብሪካ በዛሬው እለት ተመርቋል።

የዱቄት ፋብሪካውም የኦሮሚያ ክልል መክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የአርሶ አደሮች ተወካዮች በተገኙበት ነው የተመረቀው።

የኦሮሚያ የአርሶ አደሮች የህብረት ስራ ዩኒየን ፌዴሬሽን በገላን ከተማ ያስገነባው ፋብሪካው በቀን ከ1 ሺህ እስከ 1 ሺህ 500 ኩንታል የቦቆሎ ዱቄት የሚያዘጋጅ መሆኑን የኦሮሚያ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።

በ42 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው ፋብሪካው በቆሎን በመፍጨት እና እሴት በመጨመር ለገበያ የሚያቀርብ መሆኑም ነው የተገለፀው።

You might also like
Comments
Loading...