Fana: At a Speed of Life!

ከመጠን በላይ በወፈሩ ሰዎች ሳንባ ውስጥ የስብ ክምችት ይፈጠራል-ጥናት

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 10፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ከመጠን በላይ በወፈሩ ሰዎች ሳንብ ውስጥ የስብ ክምችት የሚፈጠር መሆኑን ጥናት አመላከተ።

የአውስትራሊያውይን ተመራማሪዎች ባካሄዱት ጥናት ከልክ በላይ በወፈሩ ሰዎች ሳንባ ውስጥ የስብ ክምችት የሚፈጠር መሆኑ ተረጋግጧል።

የ52 ሰዎችን ናሙና በመውሰድ በተካሄደው በዚህ ጥናት፥ ከመጠን በላይ የወፈሩ ሰዎችሳንባ ውስጥ ያለው የሳንባ ክምችት ሁኔታ እንድ ውፈረታቸው  መጠን የሚጨምር መሆኑ ተገልጿል።

ይህ በሳንባ ውስጥ የሚፈጠር የስብ ክምችትም በሳንባ ውስጥ የሚገኙ አየር ባንቧዎች ላይ ያለውን  የአየር ዝውውር ሁኔታ በመረበሽ  የእስትንፋስ ስርዓትን የሚያዛባ መሆኑ ተጠቁሟል።

በዚህ ምክንያትም ከመጠን በላይ የወፈሩ ሰዎች ለአሰምና ለተለያዩ የእስትንፋሽ ችግሮች የሚጋለጡ  መሆኑ ተመላክቷል።

ከዚህ ባለፈም በሽታው ለደም ግፊት፣ ለልብ ህመምና ተያያዥ በሽታዎች የሚዳርግ መሆኑ ነው የተገለጸው።

ስለሆነም በበሽታው የተጠቁ ሰዎች የተለያዩ ስፓርታዊ እንቅስቃሴዎችን በመስራት እና የአመጋገብ ስርዓታቸውን በማስተካከል  ሊፈጠር የሚችለውን ጉዳት መቀነስ የሚችሉ  መሆኑን ተመራማሪዎች ጠቁመዋል።

ምንጭ፦ቢቢሲ

 

You might also like
Comments
Loading...