Fana: At a Speed of Life!

ኢንስታግራም ራስን መጉዳትና ማጥፋትን የሚያስተዋውቁ ምስሎችን ከገጹ እያስወገደ ነው  

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 17፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ኢንስታግራም ደንበኞች እራሳቸውን ለመጉዳት ወይም ለማጥፋት የሚጠቀሙባቸውን የተለያዩ ዘዴዎችን ከገጹ እያስወገደ መሆኑን አስታውቋል።

አንዳንድ ማህበራዊ ትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች እራሳቸውን ለመጉዳት ወይም ለማጥፋት የሚጠቀሙባቸውን የተለያዩ ዘዴዎች በምስል በመቅረፅ በመተግበሪያዎቹ ላይ በመጫን ለጓደኞቻቸው ሲያጋሩ ይስተዋላል።

ከዚህ  ባለፈም ደንበኞች የዘመኑን ቴክኖሎጂ ውጤቶች  በመጠቀም መሰል አሰቃቂ ክንውኖችን የሚያሳዩ ካረቶኖችን በማቀናበር በማህበረዊ ሚዲያዎች ያሰራጫሉ።

ይህም የብዙ ደንበኞችን በተለይም የህፃናትና ወጣቶችን ቀልብ በመሳብ  ድርጊቱን በራሳቸው ላይ እንዲተገብሩ  እያደረገ ይገኛል።

ለአብነትም እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር 2017 ላይ ብሪታኒያዊቷ የ14 ዓመት ህፃን በኢንስታግራም ላይ ያየችውን አሰቃቂ ክንዋኔ ለመተግበር ስትሞክር ህይወቷ ማለፉ ይታወሳል።

ይህንን ችግር ለመከላከልም ማህበራዊ ሚዲያዎች በመተግበሪያቸው ላይ የሚሰራጩ ተንቀሳቃሽ ምስሎችንና ፅሁፎችን ይዘት የሚቆጣሩበት ዘዴ እንዲፈጠሩ የተለያዩ ምክረ ሃሳቦች ሲቀርቡላቸው ቆይተዋል።

ይህን ተከትሎም ኢንስታግራም በመተግበሪያው ላይ በደንበኞች የሚሰረጩ እራስን ማጥፋት ወይም መጉዳትን የሚያስተዋውቁ  ተንቀሻቃስ ምስሎችን ሆነ ካርቶኖችን ከገጹ የማስወገድ ስራን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስታውቋል

በተጨማሪም ደንበኞች መሰል ክንዋኔዎችን የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን፣ካርቶኖችን እንዲሆም ሌሎች ዘዴዎችን በመተግበሪያው እንዳይጭኑ እገዳ መስተላለፉን አስታውቋል።

ምንጭ ፦ቢቢሲ

You might also like
Comments
Loading...