Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ሞሮኮ በመድሃኒት ኢንዱስትሪ ልማት ዙሪያ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን በኢትዮጵያ የሞሮኮ አምባሳደር ኒዛ አላውአይ እና የሞሮኮ የመድኃኒት ኢንዱስትሪ ማህበር ዋና ዳይሬክተር ለይላ ላሴል ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ የመድኃኒት ምርትን ለማስፋትና ለማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት አድርገው መምከራቸው ተገልጿል።

በዚህም  ሁለቱ ወገኖች በስልጠና፣ በልምድ ልውውጥ እና የጤና ስርዓቱን በሚያጠናክሩ ሌሎች መስኮች ላይ በትብብር ለመስራት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

 

 

 

You might also like
Comments
Loading...