Fana: At a Speed of Life!

አቶ ገዱ በተመድ የፀጥታው ም/ቤት የደቡብ ሱዳን ማዕቀብ ኮሚቴ ሰብሳቢ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የደቡብ ሱዳን ማዕቀብ ኮሚቴ ሰብሳቢ አምባሳደር ጆዋና ሮኔካ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በደቡብ ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ እና በደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ወገኖች የተወሰኑ ሃይሎች ላይ የተጣለው ማዕቅብ አፈፃፀም በተመለከተ ምክክር አድርገዋል።

በአምባሳደር ጆዋና የተመራ ቡድን በምስራቅ አፍሪካ ጉብኝት ማድረጉ ከደቡብ ሱዳን ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ እድል የሚፈጥር መሆኑን አቶ ገዱ ተናግረዋል።

ኮሚቴው በደቡብ ሱዳን ሳላም እንዲሰፍን እያደረገው ያለውን እንቅስቃሴ ያደነቁት አቶ ገዱ ፥ኢትዮጵያ በደቡብ ሱዳን ሰለም እንዲሰፍን ከኮሚቴው እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት እየሰራች መሆኑን አንስተዋል።

በአሁኑ ስዓት የደቡብ ሱዳን ጉዳይ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የሚገኝ በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ተገቢውን ድጋፍ ማደርግ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

የኮሚቴው ሰብሳቢ አምባሳደር ጆዋና ሮኔካ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ በቀጠናው እና በተለይ ደግሞ በደቡብ ሱዳን ሰላም አንዲሰፍን እያደረገች ያለውን እንቅሰቃሴ አድንቀዋል።

ጠቅላይ ሚነስትር ዶክተር አብይ አህመድ የ2019 የኖበል ሰላም ተሸላሚ በመሆናቸው ደስታቸውን መግለፃቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በተጨማሪም የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ሃይሎች ከዚህ ቀደም የደረሱትን ስምምነት ተግባር ላይ በማዋል በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም በማስፈን ቁርጠኝነታቸውን ማሳየት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

You might also like
Comments
Loading...